በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ ገለጸ።

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ ገለጸ።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው እንደገለጹት በድጋፍ ሰልፉ ላይ የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ህዝቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ደጋፊነትና አጋርነት አሳይቷል ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የሠራዊቱን የሀገር ሉዓላዊነት እና የህዝብ ሰላም የማስከበር ተጋድሎ የሚያደንቁና የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ መፈክሮችንም አሰምተዋል ነው ያሉት።

እንደ ኮማንደር ዋለልኝ ገለጻ የድጋፍ ሰልፉ መርሃ ግብር ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳይገጥመው ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ሁኔታ ተጠናቋል።

የከተማዋ ህዝብ ላሳየው ከፍተኛ የሰላም ወዳድነት፣ ለጸጥታ አካላት ላደረገው ትብብርና ለሠራዊቱ ላሳየው አለኝታነት ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የድጋፍ ሰልፉን ሰላማዊነትና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የጸጥታ ኃይሉ ላከናወነው የተቀናጀና ስኬታማ ተግባር የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top