“የማይበገረው የሰላም ዘብ”

“የማይበገረው የሰላም ዘብ”

የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው!

የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ ቀን ከሌሊት በንቃት እየሰራ ይገኛል።

የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የጸጥታ ኃይሉ በአሁኑ ወቅት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ቀን ከሌሊት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለይም በሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ተግባሩን በስኬት እያከናወነ ይገኛል።

ይህ የተቀናጀ ኦፕሬሽን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍንና የማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተመልክቷል።

አሁን ላይ የአድማ መከላከል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ባደረጉት የተቀናጀ ዘመቻ የጥፋት ኃይሎችን አቅም በማዳከም ረገድ ውጤታማ ሥራ ተሠርቷል።

በቀጣይ የሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስጋት የሌለበት እንዲሆን የጸጥታ ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ቁርጠኝነት ዝግጁነቱን አረጋግጧል።

የክልሉን ህዝብ ደኅንነት በዘላቂነት ለመጠበቅና የሰላም ተጋላጭነት ያለባቸውን አካባቢዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቆጣጠር ኦፕሬሽኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የክልሉ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው በመቀጠል ሰላምን ለማጽናት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል

የሕግ ማስከበር ሥራው የክልሉን ዘላቂ ልማትና የዜጎችን ነፃነት ለማረጋገጥ ያለመ በመሆኑ፤ ሰራዊቱን በጀግንነት እና በፅናት መንፈስ የሚያንፀባርቅ ኃይል መገንባቱን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያሳውቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top