በምስራቅ ጎጃም ዞን ትንኮሳ በፈጸመው ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ ተወሰደ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳ ‘መርገጭ’ በተባለ ንዑስ ወረዳ ትንኮሳ ለመፈጸም የሞከረው ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በጥምር የፀጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተቀናጀ እርምጃ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ተገለጸ።
እንደ ፀጥታ ኃይሉ መግለጫ ታጣቂ ቡድኑ በቀን 17/ 2018 ዓ.ም በፈጸመው ትንኮሳ ሳቢያ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። ይሁን እንጂ የጥምር ኃይሉ በወሰደው ፈጣን የመልሶ ማጥቃት በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃተወስዷል።
በተጨማሪም የተለያዩ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች በፀጥታ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
የጥምር የፀጥታ ኃይሉ አካባቢውን አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ እየተቆጣጠረው እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን፣ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

