በእንጅባራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በእንጅባራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እንጅባራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ በኬላ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የጦር መሳሪያው የተያዘው መነሻውን ባህርዳር ከተማ አድርጎ ወደ እንጅባራ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው።

መረጃው እንደሚያመለክተው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 (አማ) 17657 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ኮስተር መኪና ስምንት (😎 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በተሽከርካሪው የኋላ ክፍል በሚገኝ ድብቅ ቦታ (ኪስ) በመሸሸግ ወደ ከተማዋ ሊገባ ሲል በኬላ ተቆጣጣሪዎች ተይዟል።

የእንጅባራ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር የኔው ፈቃዱ እንደገለጹት የጦር መሳሪያው ለህገ-ወጥ ታጣቂዎች ሊደርስ የነበረ መሆኑ አስታውቀዋል።

ወንጀሉን በመፈጸም የተጠረጠሩት የተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳት በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ አዛዡ አረጋግጠዋል።

ምክትል ኢንስፔክተር የኔው ፈቃዱ አክለውም የጸጥታ ስራ በአንድ አካል ጥረት ብቻ ሊሳካ እንደማይችል ጠቁመው፤ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና የህዝብን ሰላም ለማስጠበቅ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top