ለታጣቂ ቡድኖች ሊደርስ የነበረ 136 ጀሪካን ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ለታጣቂ ቡድኖች ሊደርስ የነበረ 136 ጀሪካን ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ!

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ እዝ በደብረ ታቦር ዙሪያ ባደረገው ክትትል፣ ለሕገ-ወጥ ታጣቂዎች ሊተላለፍ የነበረ 136 ጀሪካን ነዳጅ እና የሞተር ዘይት ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ሕገ-ወጥ ነዳጁን እና የሞተር ዘይቱን በአንድ አይሱዙ ተሽከርካሪ በመጫን ከደብረ ታቦር ወደ ወረታ በሚወስደው መንገድ ላይ ለማሳለፍ ሲንቀሳቀሱ ቀድሞ ስምሪት በተሰጣቸው የሠራዊቱ አባላት መያዛቸው ተገልጿል።

መንግሥት በአሁኑ ወቅት ያለውን የነዳጅ ሥርጭት ችግር ለመፍታትና ፍትሐዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን አውጥቶ እየሠራ ባለበት ወቅት ግለሰቦቹ ነዳጁን በጀሪካን በመደበቅ ለታጣቂ ቡድኖች ለማቅረብና ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረቱን ለማባባስ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ከእዙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምሥራቅ እዝ በተሰጠው የሕግ ማስከበር የግዳጅ ቀጠና ውስጥ ከአካባቢው የጸጥታ አካላት እና ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን የመከላከል እና የማክሸፍ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እዙ በዝርዝር አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top