በወልዲያ ከተማ ዳቦ ቤት ኬላ 102 ጀሪካ ናፍጣ የጫነ የጭነት መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ

በወልዲያ ከተማ ዳቦ ቤት ኬላ 102 ጀሪካ ናፍጣ የጫነ የጭነት መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ

ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴና የኮንትሮባንድ መስፋፋት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ከ102 ጀሪካ በላይ ናፍጣ በህገ-ወጥ መንገድ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር (FSR) የጭነት መኪና በቁጥጥር ስር መዋሉን የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አበራ ካሳው እንደገለጹት፣ መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ወደ መስመር ሲጓዝ የነበረው ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 25975 አ.አ የሆነ የጭነት መኪና በቁጥጥር ስር የዋለው በደረሰ ጥቆማ መሠረት ነው።

መኪናው በላዩ ላይ በርከት ያለ ፍራሽና የሞተር ዘይት ጭኖ የነበረ ቢሆንም በውስጡ ተደብቆ የተገኘው ህገ-ወጥ ነዳጅ መሆኑ ታውቋል።

በወልዲያ ከተማ ‘ዳቦ ቤት’ ተብሎ በሚጠራው የፍተሻ ኬላ ላይ በተደረገ ጥንቃቄ የተሞላበት ፍተሻ እያንዳንዳቸው 25 ሊትር የሚይዙ 102 ቢጫ ጀሪካ ናፍጣ ተገኝቷል።

ኮማንደር አበራ ካሳው አክለውም ግለሰቦች የተለያዩ መሸፈኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ መሰማራታቸው የሚያሳዝን ነው።

ፖሊስ እንዲህ ያሉ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት በኬላዎች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ይህ የነዳጅ ምርት በህገ-ወጥ መንገድ ተደብቆ መጓዙ በኢኮኖሚው ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ ለከፍተኛ የእሳት አደጋ ስጋት የሚዳርግ መሆኑም ተመልክቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top