በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአመራሮች የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም መለኪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአመራሮች የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም መለኪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተቋሙን አመራሮች የአሠራር ብቃት ለማሳደግና ተልዕኮን በውጤት ለመመዘን የሚያስችል የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም መለኪያ ዙሪያ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።

በዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክቶሬት ከደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሥልጠና ተቋማዊ ግቦችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመለካትና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የሥልጠና መርሃ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ ተቋሙ የሰው ኃይሉን በየጊዜው በተለያዩ ሥልጠናዎች በማብቃት ረገድ ሰፊ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋማዊ ስኬትን ለማረጋገጥ ዘመናዊና አዳዲስ የአሠራር ሥርዓቶችን መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ ጠቁመዋል።

እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አመራር በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ራሱን በማብቃት ተቋሙ የሚጠብቅበትን ኃላፊነት በብቃት መወጣት ይኖርበታል ሲሉም አሳስበዋል።

በተለይም እንደ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ያሉ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ለአመራሩ የሚሰጧቸው መሰል ሥልጠናዎች የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ከመፈጸም አኳያ የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው አስገንዝበዋል።

አመራሩ ራሱን በዕውቀት በማሳደግ ተቋሙን በሚመጥን መልኩ ዝግጁ እንዲሆን በማድረግ እና ለተቋማዊ ዕድገት መሠረት መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ ጠቁመዋል።

ይህ የአመራር አቅም ግንባታ ሥልጠና ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በመጨረሻም አመራሩ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ውጤትን መሠረት ያደረገ የአፈጻጸም ምዘና ሥርዓት እንዲከተል ያስችለዋል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top