በሰሜን ጎጃም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እጅ ሰጡ።

በሰሜን ጎጃም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እጅ ሰጡ።

በሰሜን ጎጃም ዞን ባህርዳር ዙሪያና ሰሜን ሜጫ አካባቢ በተሳሳተ መንገድ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች፣ መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ በመቀበል በምህረት ወደ ህዝባቸው ተቀላቅለዋል።

በአስር አለቃ ቻላቸው አስናቀ (ቻቻ) እና ቢኒያም ጋሻው የሚመሩት የቡድኑ አባላት መርዓዊ ከተማ ሲደርሱ በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዛሬው ዕለት ከነሙሉ ትጥቃቸው እጅ የሰጡት ዋና ዋና አመራሮች፦

10 አለቃ ቻላቸው አስናቀ (ቻቻ) – (የቀድሞ የ102ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ)

ቢኒያም ጋሻው – የብርጌድ ዘመቻ መምሪያ

ጋሻው መኳንት – የ11ኛ ክፍለ ጦር የሰው ኃይል ኃላፊ

ዘላለም አዱኛ – የቅንባባና አካባቢዋ ሻለቃ ኦርዲናንስ

እንዳላማው ገብሬ – የቅንባቤ ሻለቃ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ

ጋሻ ታደለ – የደጉ በላይ ሻለቃ መሪ እና እነዚህን አመራሮች ጨምሮ በአጠቃላይ 22 የቡድኑ አባላት በሰላም እጃቸውን በመስጠት ወደ ህዝብ ተቀላቅለዋል።

ታጣቂዎቹ ለመንግስት እጅ የሰጡት ከነሙሉ ትጥቃቸው ሲሆን፣ ያስረከቧቸው የጦር መሳሪያዎችም

1 ብሬን፣ 11 ክላሽን ኮቭ፣ 2 ኤስ.ኬ.ኤስ (SKS)፣ 2 ፋል (FAL) እና 4 ቦንቦች ሲሆኑ 242 የክላሽ ጥይት፣ 95 የብሬን ጥይት፣ 19 የM14 ጥይት እንዲሁም 34 ልዩ ልዩ ካዘናዎች ፣1 የመገናኛ ሬዲዮ እና 9 የደረት ትጥቆች ገቢ ሆነዋል።

በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ ወጥተው እንደነበር የገለጹት አስር አለቃ ቻላቸው አስናቀ (ቻቻ)፣ ከሻቢያና ከህወሃት ጋር አብሮ መስራት ህዝባችንን ይባስ መበደል መሆኑን በመረዳታችን ሰላምን መርጠናል፤ የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top