በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ቅሬታ ያላቸው የሰራዊቱ አባላት እና ማህበረሰቡ ሀሳባቸውን የሚያቀርቡበትን ግልጽ የአሰራር ስርዓት ተመቻችቷል።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ቅሬታ ያላቸው የሰራዊቱ አባላት እና ማህበረሰቡ ሀሳባቸውን የሚያቀርቡበትን ግልጽ የአሰራር ስርዓት ተመቻችቷል።

ተቋሙ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ እና ቅሬታ ያላቸው የፖሊስ አባላትና ሌሎች ግለሰቦች ጥያቄና ቅሬታቸውን በማቅረብ ከሚመለከተው አመራር መፍትሔ የሚሰጥበትን አሰራር መጀመሩን በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ተናገሩ።

አሰራሩ ፖሊስ ተቋሙ ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው የሚሉት ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ በተቋሙ አሰራር ዙሪያ ቅሬታና የመብት ጥያቄ ያለው ማንኛውም አካል ዘወትር ማክሰኞና ሀሙስ ከጧቱ 3ሰዓት ጀምሮ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ዋናው አዳራሽ በመቅረብ ጉዳዩን በማስረዳት ከሚመለከተው አካል ምላሽ ማግኘት ይችላል ብለዋል።

ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው ይህ ተግባር የባለ ጉዳይን ጊዜ እና ገንዘብ ለመቆጠብና የሚመለከተውን አመራር የተጠያቂነት አሰራርን ለማስፈን የሚያስችል በመሆኑ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች በግልጽ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የመልካም አስተዳደር ቅሬታ ሰሚ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር መዓዛ ዋለልኝ በበኩላቸው የክልሉ ፖሊስ ተቋም ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የፖሊስ አባላትን ቅሬታ በተቀላጠፈ መንገድ ለመፍታት ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል ይህ አሰራር አንዱ ሲሆን ቅሬታ አቅራቢዎች ያለምንም ወጭና እንግልት በየ ዞንና ወረዳቸው ቅሬታዎችን በማቅረብ ምላሽ ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ስለመኖሩ ገልፀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎች እና ምላሽ የሚሰጡ አመራሮች በተገኙበት የሚደረግ የሀሳብ ልውውጥ በመሆኑ ግልፅ ለሆኑ ቅሬታዎች ግልፅ እና ፈጣን የሆነ ምላሽ ይሰጥበታል ያሉት ኮማንደር መዓዛ ማንኛውም ቅሬታ አለኝ የሚል አካል በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመቅረብ ምላሽ ማግኘት የሚችል መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top