የደቡብ ጎንደር ዞን የጥፋት ቡድኑን ተልዕኮ ያከሸፉ የጸጥታ ኀይሎችን አመሠገነ።

የደቡብ ጎንደር ዞን የጥፋት ቡድኑን ተልዕኮ ያከሸፉ የጸጥታ ኀይሎችን አመሠገነ።

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ በታሪካዊቷ የደብረ ታቦር ከተማ ላይ የተሰነዘረውን የጥፋት ተልዕኮ በብቃት ላከሸፉ የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው እንደገለጹት ህገ-ወጥ ታጣቂው ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር የነገሥታት መናገሻ የኾነችውን ደብረ ታቦርን ለማውደም እና ሀገርን ለማዋረድ የያዘው የባንዳነት ተልዕኮ በአማራ አድማ መከላከል ፖሊስ፣ በዞኑ እና በከተማዋ የጸጥታ መዋቅር የተቀናጀ ጥረት ከሽፏል።

ህገ-ወጥ ቡድኑ የሕዝብ ተቋማትን እና የግለሰብ ቤቶችን በማቃጠል አማራ ጠልነቱን ዳግም ማረጋገጡንም ገልጸዋል። ጽንፈኝነት ያለአቅም ድልን የመመኘት አባዜ መኾኑን ጠቅሰዋል። ቡድኑ ተልዕኮውን ከሕወሓት እና ከሻዕቢያ በመቀበል እንደ ፈረስ እየተጋለበ ያለ የጥፋት ኀይል ነው ብለዋል።

የቡድኑን እኩይ ዓላማ ላከሸፈው የጸጥታ ኀይል ምሥጋና አቅርበዋል። በየጫካው የሚገኙ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ሀገርን ከመሸጥ ወጥተው የመንግሥትን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል አድማ መከላከል 1ኛ ሻለቃ አዛዥ ኢንስፔክተር አስማማው ብርሃኔ የተከናወነው ግዳጅ “ሀገርን ያኮራ እና ጠላትን ያሳፈረ” መኾኑን ገልጸዋል።

“እኛ የምንዋጋው ለሕዝብ ነው፤ ጠላት ግን የሚዋጋው የእናቱን ሞሰብ ገልብጦ ለጠላት ለመስጠት ነው” ያሉት አዛዡ በጋራ በተደረገ ኦፕሬሽን ዘራፊው ቡድን ተመትቶ ሙት እና ቁስለኛ ኾኖ እግር አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል ነው ያሉት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top