በተጠናከረ የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ተግባር በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን የመርዓዊ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

በተጠናከረ የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ተግባር በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን የመርዓዊ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

ላለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ችግሮችን ካስተናገዱ የክልሉ አካባቢዎች መካከል የሰሜን ጎጃሟ መርዓዊ ከተማ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

ይህን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍም በተሰሩ የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ስራ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም መምጣቱን በሰሜን ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉ ማህሙዴ ተናግረዋል።

ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉ ማህሙዴ እንደሚሉት ቀደም ባሉት ዓመታት መርዓዊ ከተማ ከወቅታዊ የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት የነበረችና የትምህርት፣የጤና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ተቋርው የነበረባት ከተማ ነበረች ብለዋል።

አሁን ላይ ችግሩን ለመቅረፍ የከተማዋ ፖሊስ ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ባደረጉት የወንጀል መከላከልና የህግ ማስከበር ስራ አንፃራዊ ሰላም ማምጣት ተችሏል ነው የሚሉት አዛዡ።

የትምህርት፣የጤና፣የንግድ እንቅስቃሴ እና ሌሎች የግል እና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ በመጀመራቸው ማህበረሰቡ ተጠቃሚ መሆኑንም አዛዡ አክለው ገልፀዋል።

ለሰላሙ ዋጋ የሚሰጥ ማህበረሰብ ተፈጥሯል የሚሉት ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉ አሁን ላይ የከተማዋ ፖሊስ እና ማህበረሰብ ተደጋግፎ እየሰራ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top