በሰሜን ሸዋ ዞን መሐል ማማ ወረዳ በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
በሰሜን ሸዋ ዞን በመሀል ማማ ወረዳ ባሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመንግስት ጥምር ጦር ባከናወነው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ።
በዛሬው ዕለት በተከናወነው በዚህ ወታደራዊ እርምጃ 13 የታጣቂ ቡድን አባላት የተደመሰሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ዘውዱ የተባለ የሻለቃ መሪ እንደሚገኝበት ታውቋል። በተጨማሪም 2 የቡድኑ አባላት ተማርከዋል።
በኦፕሬሽኑ ወቅት ከታጣቂዎቹ እጅ የተያዙ የጦር መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።
የተያዙ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፦
1 ብሬን እና 1 ተጨማሪ የብሬን አፈሙዝ
2 ስናይፐር መሳሪያዎች
7 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች
1 ኤምፎርቲ (M40)
1 ቺቺ መሳሪያ እና 1 መገናኛ ሬዲዮ
የተያዙ ጥይቶችና ሌሎች ትጥቆች፦
1,914 የብሬን ጥይት እና 361 የክላሽ ጥይት
3 የብሬን ሸንሸል (አንድ ባለ 200 እና ሁለት ባለ 100)
4 ኤፍ-ዋን (F1) ቦንቦች፣21 የክላሽ መጋዘን እና 3 የስናይፐር መጋዘን እና የወገብና የደረት ትጥቆች ጥምር ጦሩ ኦፕሬሽኑን በስኬት ማጠናቀቁን የገለጸ ሲሆን፣ በጸጥታ ኃይሉ በኩል ምንም ዓይነት የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጧል።
በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።








