በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የእንጅባራ ከተማን ሰላም ለማፅናት የከተማዋ ፖሊስ ማህበረሰቡን ባለቤት ያደረገ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የማህበረሰብ ዓቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ደሳለው እንደተናገሩት የከተማዋ ማህበረሰብ ሰላም ወዳድና ወንጀል ጠል በመሆኑ ሰላማችን በእጃችን በሚል መርህ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተጠናክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥም ከማህበረሰቡ እና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተን እየሰራን ነው ሲሊ ተናግረዋል።
የእንጂባራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የህዝብን ሰላም ለማስከበርና የመልካም አስተዳደር ችግርን ለማስቀረት ቁርጠኛ ነው የሚሉት ኢንስፔክተሩ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት በቀንና በማታ ይፈጸሙ የነበሩ የዝርፊያ፣እገታና መሰል ወንጀሎችን መቀነስ ተችሏል ብለዋል።
ማህበረሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን ተሰልፎ ወንጀልን ለመከላከል እና ሰላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ላለው ከፍተኛ ስራ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በምሽት የአካባቢ ጥበቃ ስራ እየሰሩ ያገኘናቸው የከተመዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ሰላማችን የራሳችን ትልቅ ፀጋ በመሆኑ በፖሊስ አስተባባሪነት በራሳችን ጥረትና ትጋት የመጠበቅ ግዴታ ስላለብን ከተማችንን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ ቁርጠኞች ነን ብለዋል።
ለህዝባችን ሰላም ሌት ከቀን የሚተጋው የከተማችን ፖሊስ ክብር ይገባዋል ያሉት ነዋሪዎቹ ፖሊስ ለወንጀል መከላከል ስራ ቀዳሚ ተዋናይ ቢሆንም ብቻውን ውጤት ማምጣት ስለማይችል ሁሉም ማህበረሰብ አካባቢውን በመጠበቅና ለፀጥታ ሀይሉ አይንና ጆሮ በመሆን ወንጀልና ወንጀለኛን ማስቀረት ያሰፈልጋል ብለዋል።
ማህበረሰቡን ከተሳታፊነት ወደ ባለቤትነት ያሻገረ የወንጀል መከላከል አሰራር በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።