በደብረ ታቦር ከተማ የሚከበረው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የተቀናጀ የፀጥታ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።

በደብረ ታቦር ከተማ የሚከበረው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የተቀናጀ የፀጥታ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።

ነገ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የሚከበረውን የቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም እንዲከበር የከተማዋ ፀጥታ ኃይል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በደብረ ታቦር ከተማ በመገኘት ለፀጥታ ግብረ-ኃይሉ የስምሪት መመሪያ ሰጥተዋል።

በዓሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የሚታደምበት በመሆኑ፣ የፀጥታ ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃትና በከፍተኛ ዲሲፕሊን ተረባርቦ ሰላምን እንዲያስከብር አሳስበዋል።

ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት ቀድሞ መከላከል በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ትኩረት እንዲደረግና ከማኅበረሰቡ ጋር በቅርበት በመቀናጀት ስምሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን መመሪያ አስተላልፈዋል።

የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች በመረጃ ልውውጥና በጋራ ኦፕሬሽን ረገድ ያላቸውን ትስስር በማጠናከር፣ የበዓሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ከሌሎች የፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

ወደ በዓሉ ቦታ በሚገቡ ምእመናንና እንግዶች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እንደሚደረግና በከተማዋ መውጫና መግቢያ በሮች ላይ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

በበዓሉ አካባቢ የሚኖረውን የሰውና የተሽከርካሪ ግርግር ለመቀነስ ጊዜያዊ የመንገድ ዝግጅቶችና የትራፊክ ፍሰት ማስተካከያ ተደርጓል ሲሉም አክለዋል።

እንግዳ ተቀባይ የሆነው የደብረ ታቦር ከተማ ህዝብም ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top