የ86ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ቀን በሰላም ተጠናቋል።

የ86ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ቀን በሰላም ተጠናቋል።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ቀን በዓል ዘንድሮም ለ86ኛ ጊዜ”የአብሮነት ቅርስ፣የሰላም ውርስ” በሚል መሪ ቃል በእንጂባራ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የክልሉ የፀጥታ አካላት ከፌዴራል የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መስራቱን በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአድማ መከላከል ፖሊስ ምክትል ዋና መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ልጅ አዱኛ ሙሉጌታ ተናግረዋል።

እንደ ኮማንደር ልጅ አዱኛ ሙሉጌታ ገለፃ በዓሉ ከሀገር ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና እንግዶች በተጨማሪ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የታደሙበት ታላቅ በዓል በመሆኑ የክልሉ አድማ መከላከል ሰራዊቱ ውጤታማ የህግ ማስከበር ተግባር መወጣቱን ገልጸዋል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በኬላ ፍተሻ፣በአካባቢ ጥበቃ፣ ሰርጎ ገብነትን በመከላከል፣ ልዩ ልዩ የዘረፋ፣የማታለል እና የማጭበርበር ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ቅድመ ዝግጂት በማድረግ ከፍተኛ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በዓሉ በሰላም ተጠናቆ እንግዶች ወደመጡበት እስኪመለሱ ድረስ ከፍተኛ ጥበቃና የወንጀል መከላከል ስራ ከአጋር የጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ የወንጀል መከላከል ስራን በስኬት አከናውኗል ብለዋል።

በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ወጣቱ፣የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ድጋፍና ትብብር በክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top