የ”መብረቁ ብርጌድ” ታጣቂዎች በሰላም እጃቸውን ሰጡ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አካባቢ ራሱን “መብረቁ ብርጌድ” በማለት ሰይሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የታጠቀ ቡድን በሰላም ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅሏል።

ይህ ቡድን በሰላም እጁን ሊሰጥ የቻለው በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

የሰላም ስምምነቱን ተቀብለው ከነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም የገቡትን ታጣቂዎች የአካባቢው አመራሮች ተቀብለዋቸዋል።

ቡድኑ ከነ ሙሉ ትጥቁ በሰላም ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀለ ሲሆን፣ ይህም በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top