በቻግኒ ከተማ ከ2 ሺ 600 በላይ ህገ ወጥ የክላሽ ጥይት ተያዘ፤
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከ2600 በላይ ህገ ወጥ የክላሽ ጥይት ተይዟል።
መነሻዉን ጃዊ ወረዳ ያደረገ ታርጋ ቁጥር ኮድ 24372 አ.ማ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ራንች ኬላ ላይ በከተማዉ የመረጃና ደህንነት ባለሙያ እንዲሁም በፀጥታ ሀይሎች በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር 2 ሺ 694 ፍሬ ህገ ወጥ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
በከተማዉ ያለዉን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር ለማስቀረት የቻግኒ ከተማ የመረጃና ደህንነት ባለሙያዎች እንዲሁም አጠቃላይ የፀጥታ ሀይሎች እየሰሩት ላለዉ ስራ ከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርቧል።




