በክልሉ መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በታች ጋይንት ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ገቡ።

በክልሉ መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በታች ጋይንት ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ገቡ።

በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰውን አዲስ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀስ የቆየው እና እራሱን የገብርየ ክፍለ ጦር በማለት ሲጠራ የቆየው ቡድን የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ገብቷል።

ውሳኔው በክልሉ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የትጥቅ ግጭት በውይይት ለመፍታት የተያዘውን አዲስ አቅጣጫ በተግባር መሬት ያወረደ ትልቅ እርምጃ ኾኖ ተመዝግቧል።

​በተዘጋጀው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top