በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የጸጥታ አካላት ባከናወኑት የተቀናጀ ኦፕሬሽን 12 ኩንታል ሓሽሽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ አስታውቋል።
ኮማንደር ወለላው ተገኘ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንዳስታወቁት ዕፁ የተያዘው ህገ-ወጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተደረገ ጥብቅ ክትትል ሲሆን፤ ይህም በአካባቢው ማህበረሰብ ደህንነትና ጤና ላይ ሊደቀን የነበረውን ከፍተኛ አደጋ ለማስቀረት አስችሏል ብለዋል።
በተጨማሪም በግለሰቦች በመኖሪያ ቤት ውስጥ ማጠቢያ በመትከል ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ ወርቅ ሲያጥቡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ሲሉ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ አክለው ገልጸዋል።
በድርጊቱ ላይ ተሰማርተው የተገኙ ተጠርጣሪዎችና ለስራው ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የወርቅ ማጠቢያዎች በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
እንደ ኮማንደር ወለላው ገለጻ እንዲህ አይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ እና በአካባቢው ሰላም ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመከላከል ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ህብረተሰቡም መሰል አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በማጋለጥ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር እንዲያጠናክር ኮማንደር ወለላው ተገኘ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ጥሪ አቅርበዋል።
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን 12 ኩንታል ሓሽሽና ህገ-ወጥ የወርቅ ማጠቢያ በቁጥጥር ስር ዋሉ።