የአማራ ክልል ፖሊስ የከተራና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ።

የአማራ ክልል ፖሊስ የከተራና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ።

የከተራና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርባል።

የክልሉ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ በየአመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ባማረና በደመቀ መልኩ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ለዚህ የጸጥታ ስራ ስኬት የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብር-ኃይል የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በመቀናጀት በዓሉ ባማረና በደመቀ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣታቸውን ገልጸዋል።

ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ የሐይማኖት አባቶች ትልቅ አክብሮት አለን ብለዋል።

በተለያዩ የክልሉ ከባቢዎች በዓሉ በሰላም እንዲከበር እና ለበዓሉ ድምቀት መላው የክልሉ ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ለተወጡት ኃላፊነት ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top