የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የ6 ወር የስራ አፈጻጸምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ግምገማ እና ውይይት አካሂደ።

የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የ6 ወር የስራ አፈጻጸምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ግምገማ እና ውይይት አካሂደ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ በስሩ ከሚገኙ የዋና መምሪያ፣ የመምሪያ፣ የዋና ክፍል እና ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ገምግሟል።

በግምገማው የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ እንደተናገሩት የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የተቋሙ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ በተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችና በሌሎች መደበኛ ተግባራት በኩል ባለፉት 6 ወራት በርካታ ተግባራትን ፈፅሟል ብለዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ገለፃ በግማሽ ዓመቱ ከሰው ሀይል ግንባታ፣ከሪፎርም አፈፃፀም፣ ከበጀት አስተዳደርና ሎጀስቲክ አጠቃቀም አንፃር በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆኖ ተቋሙን የሚያሻግሩ ስራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

በቀጣይም ፖሊስ ተቋሙን ተወዳዳሪ እና ተራማጅ ለማድረግ ለውጥ መር አስተሳሰብ ማምጣት፣ የአመራር ሚናን ለመወጣት የሚያስችል ብቃት መላበስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ የማስቀጠልና ስራን ቆጥሮ ሰጥቶ የመቀበል ልምድን ማዳበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በትኩረት ከሚሰሩ የቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ስለመሆናቸውም ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ አብራርተዋል።

ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው በክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው ዋና መምሪያው ባለፉት 6 ወራት ከክልል እስከ ዞን ከዘለቀ የአመራርና ባለሙያ የሰው ሃይል ግንባታና ምደባ በተገቢው ሁኔታ በከናወኑን ተናግረዋል።

ለክልሉ ፖሊስ ለሰራዊት አመራር እና አባላት በተለያዩ ዘርፎች የስራ ላይ ስልጠና፣ የጂኦስትቴጂካዊ ስልጠናና ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር የትምህርት ዕድል መሰጠቱን አክለው ገልፀዋል።

ከሰው ኃይል መረጃ አያያዝ በኩልም ቀደም ሲል ከነበረው አድካሚና ያልተደራጀ አያያዝ በመውጣት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን መከተል ተጀምሯል ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት አብራርተዋል።

ጠቅላይ መምሪያው ስር ያሉ ሁሉም ዘርፎች ያከናወኗቸው ተግባራት ተቋሙን የሚያሳድጉ እና ለቀጣይ ተግባራት መነሻ የሚሆኑ መሆናቸውን ገልፀው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሪፎርሙ መሪ እና ፈፃሚ የሆነ የፖሊስ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችሉ መሆናቸውን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top