ባለፉት 6 ወራት ከ9 ሺህ 5 መቶ በላይ የክስ መዝገቦች ቀርበው ከ7 ሺህ 1 መቶ በላይ መዝገቦች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልኳል።

ባለፉት 6 ወራት ከ9 ሺህ 5 መቶ በላይ የክስ መዝገቦች ቀርበው ከ7 ሺህ 1 መቶ በላይ መዝገቦች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልኳል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከክልል እና ከዞን የወንጀል ምርመራ አመራሮችና አባላት ጋር የግማሽ ዓመቱን የስራ አፈጻጸም በበይነ መረብ ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ የወንጀል ምርመራ ስራዎች ለቀጣይ ተልዕኳችን ድክመቶቻችንን አርመን ጥንካሬዎቻችንን የምናስቀጥበት ይሆናል ብለዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ገለፃ ባለፉት 6 ወራት የሰዎች እገታና የታጠቁ ቡድኖች የወንጀል ተግባራት፣ የኢኮኖሚ ወንጀሎች እና የኮንትሮባንድ ድርጊቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመሰረቱ የሳይበር ወንጀሎች ምርመራ ስራው ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥረው የነበሩ ጉዳዮች ቢሆንም ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በተሰራ ስራ ጥሩ አፈፃፀም ተመዝግቧል ብለዋል።

ከመደበኛ የወንጀል ምርመራ በተጨማሪም ህገወጥ የመሬት ወረራና የመንግስት ንብረት ምዝበራ ጋር በተያያዘ በርካታ መዝገቦችን በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

የተቋሙ የሪፎርም አካል የሆነው የተጠርጣሪ ማቆያ ክፍል ግንባታና የፎረንሲክ ምርመራ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለወንጀል ምርመራ ስራው ትልቅ ግብዓት ሆነዋል ሲሉም አክለዋል።

የወንጀል ምርመራ ሙያ ህዝብን እና መንግስትን የሚያስተሳስር እና ታዓማኒነትን የሚያጠናክር ሙያ በመሆኑ ስራችን ሳይንሳዊ፣ ፍትሐዊ እና በበቂ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል።

በበይነ መረብ ግምገማውም በሰብዓዊ መብት አከባበር እና እያያዝን በተመለከተ በቴክኖሎጂ የታገዘ የወንጀል ምርመራ አሰራርን ከማሳደግ እና ተጠያቂነት እና ግልፀኝነት ላይ ያተኮረ ስራን ከመስራት አኳያ ባሉ ውስንነቶች ዙሪያ ከተለያዩ ዞኖች ሀሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ባለፉት 6 ወራት ከ9 ሺህ 5 መቶ በላይ የክስ መዝገቦች ቀርበው ከ7 ሺህ 1 መቶ በላይ መዝገቦች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩንም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም እንደተመዘገበም ሪፖርቱ ያመላክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top