የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ያሰለጠናቸዉን የመንገድ ላይ ትራፊክ ተቆጣጣሪና የወንጀል መረጃ ክትትል ባለሙያ ሰልጣኝ ፖሊሶች አስመረቀ፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ያሰለጠናቸዉን የ15ኛ ዙር የመንገድ ላይ ትራፊክ ተቆጣጣሪና የ4ተኛ ዙር የወንጀል መረጃ ክትትል ባለሙያ ሰልጣኝ ፖሊሶችን አስመርቋል፡፡
የምረቃ መርሃ ግብሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሸነር አበበ ደለለ እና የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ስተራቴጂክ አመራሮች እንዲሁም መምህራንና አሰልጣኞች በተገኙበት ተካሄዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የስልጠና ሪፖርት ያቀረቡት የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ የአካዳሚክስ ጉዳዩች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሸነር ግዛቸው ከበደ ሰልጣኞቹ በስልጠና ቆይታቸው በርካታ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ትመህረቶች እንዳገኙ አንስተው በቀጣይ ይህንን ተግባር በመጠቀም የክልሉን ማህበረሰብ በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዪኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ እንደተናገሩት ዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ1985 ዓ/ም ጀምሮ የተለያዩ የአመራር፣ ልዩ ልዩ እና መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠናዎችን በመስጠት ለክልሉ መንግስተ እና ህዝብ በማስረከብ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን አንስተዋል።
ዩኒቨርሰቲ ኮሌጁ በክልሉ የተጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ይሆን ዘንድ የፈጻሚ አካላትን አቅም በመገንባት የፖሊስ ተቋም በዕዉቀት ላይ ተመስረቶ እንዲመራ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የክልላችንን የትራፊክ ፍሰት ለመቆጣጠር እና የተጠናከረ የመረጃ ቅብብሎሽን ለማጎልበት የዚህ ዙር ስልጠና ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
እንደ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ ገለጻ አሁን ክልላችን ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ ሙያዊ ስልጠና የተሰጠ በመሆኑ በምትመደቡበት አካባቢ የተሰጣቸውን ሙያዊ ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር የተጣለባችሁን ኃላፊነት በብቃት እንድትወጡ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዕለቱ ተመራቂዎች በበኩላቸዉ የወሰዱትን ሙያዊ ስልጠና በመጠቀም የክልሉን ማህበረሰብ ለማገልገል እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ለስልጠናዉ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና በስልጠና ቆይታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡












