የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በየደረጃው የሚገኝ የጸጥታ ኃይል የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለበት ተባለ።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በየደረጃው የሚገኝ የጸጥታ ኃይል የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለበት ተባለ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በ2018 ዓ.ም የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የሚያስችል ልዩ የበዓል እቅድ ውይይት ከፀጥታ ግብረ-ሀይሉ ጋር አድርጓል ።

በውይይቱ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ከፀጥታ ግብረ-ኃይሉ የተውጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ

በሀገራችን በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩ ህዝባዊ በዓላት መካከል ጥምቀት አንዱ በመሆኑ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲውል የፀጥታ ግብረ-ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

የጸጥታ ግብረ ኃይሉ ያወጣውን እቅድ በቁርጠኝነት እና በቅንነት መፈጸም የእያንዳንዱ የጸጥታ ኃይል ኃላፊነት በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

ወደ ከተመዋ የሚመጡ ቱሪስቶች ንብረታቸውን እንዳይዘረፉ ሰላማቸው ተጠብቆ በዓልን አክብረው ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ የተጠናከረ የወንጀል መከላከል ስራ መስራት እንደሚገባም ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ አሳስበዋል።

ቋሚ ጥበቃ ሊደረግባቸው በሚገቡ ቦታዎች ላይ ተመጣጣኝ እና የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል በመመደብ የቅድም ወንጀል መከላከል ስራ መስራት የሚያስችል እቅድ በመሆኑ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ገለጻ ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት በመመስረት የወንጀል መከላከል ተግባሩን ለማህበረሰቡ በባለቤትነት በመስጠት ሰላሙ የኔ ነው ብሎ እንዲያምን እና የተደራጀ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር በየደረጃው የሚገኝ የጸጥታ ኃይል የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበትም አሳስበዋል።የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴወድሮስ በጥምቀት በዓል በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎች ወደ ከተመዋ ስለሚገቡ ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡን ለመረበሽ እና በዓሉ በሰላም እንዳይከበር ህገ-ወጥ ተልዕኮ ይዘው የሚመጡ አካላትን ለመከላከል ከፀጥታ ግብረ ኃይሉ በተጨማሪ ወጣቱን፣ማህበራትን ፣የሀይማኖት አባቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በማወያየት ወደ ስራ የሚያስገባ እቅድ አውጥተን ወደ ተግባር መገባቱንም ጠቁመዋል።

በዓሉን ለማክበር በርካታ እንግዶች ወደ ከተመዋ ስለሚገቡ ኬላዎችን ፣አልጋ ቤቶችን እና መጠጥ ቤቶችን በጥንቃቄ የሚፈተሽና ክትትል የሚያደርግ እና ማህበረሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ የሚያስችል እቅድ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በከተማው በየሰፈሩ እና በየብሎኩ ማህበረሰቡን በማደራጀት የመረጃ ልውውጦችን በማጠናክር እና የድንገተኛ አሰሳ በማድረግ ሰርጎ ገቦችን የመለየት ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እና አደጋ እንዳይከሰት ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር በቅንጅት መስራት የሚያስችል እቅድ ውይይት በማድረግ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።

በጥምቀት በዓሉ ላይ የትኛውም ህገ-ወጥ ተግባር ቢፈጸም ለፈፀመው ተግባር በስቸኳይ ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኝ ጊዜያዊ የምርመራ እና ችሎት የተቋቋመ መሆኑንም አዛዡ ጠቁመዋል።

ታቦታት የሚያርፉበትን ቦታ ቀድሞ በመፈተሽ እና ያለምንም ችግር እንዲመለሱ የሚያስችል በቂ እና የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል እንደተዘጋጀም ጠቁመዋል።

ተወያይ አመራሮች በበኩላቸው የፀጥታ ኃይሉ በታማኝነት፣ በቅንነትና በሀላፊነት በመስራት በዓሉን ሊያከብሩ የሚመጡ እንግዶች ያለምንም ችግር እና መጉላላት ለመጡበት ዓላማ መንቀሳቀስ እንዲችሉ የጸጥታ ግብረ-ኃይሉ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሚያሳይ እቅድ እንደሆነ ጠቁመዋል።

አፈናዎችን ንጥቂያዎችን እና ዝርፊያቸዎችን ለመከላከል የጸጥታ ኃይሉ ከአጋር አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት የሚያስችል ውይይት እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ፈጣን እና የተደራጀ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ከፀጥታው ግብረ ኃይል ጋር በመቀናጀት ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ የቅድመ ወንጀል መከላከል ተግባር ለማከናወን የሚያስችል መሆኑንም አረጋግጠዋል ።

የተቋቋመው ጊዜያዊ የምርመራ እና ችሎት ለተበደለው ፈትህ ለበደለው ደግሞ ተገቢውን ቅጣት ለመስጠት ተነጋግሮ እና ተግባብቶ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ፖሊስ መምሪያው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

ፖሊስ መምሪያው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ሰላም ማህበር፣ የጫኝና አውራጅ ማህበር ፣ባጃጅ ማህበር ፣ ደላላ ማህበር ፣ፋሲል ከነማ ማህበር ፣ ሸራ አጋዥ ማህበር እና አነቃቂ ማህበር ጋር የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ነው ውይይት ያደረገው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ በምታደርጓቸው እያንዳንዱ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በንቃት እና በትኩረት በመስራት ከተማችሁ የሰላም ባለቤት እንደሆነች በዓሉን ሊያከብሩ ከየትኛውም አለም ለሚመጡ እንግዶች ማሳየት ይኖርብናል።

ለጎንደር ከተማ ሰላም መስፈን የወጣቱ ሚና የጎላ ነው ያሉት አዛዡ ማህበረሰቡን በማደራጀት ለሰላም እንዲዘምር እና የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን መስራት ይኖርባችሗል ብለዋል።

የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱ ፈጣን እና ተደራሽ መሆን እንደሚኖርበትም ተጠቁሟል።

ሰላምን ለመጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጎን ሆናችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁት ስራ ውጤታማ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የከተማችንን ሰላም ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ዝግጅት አድርገናል ያሉት ደግሞ የማህበራት አመራሮች ሲሆኑ የክልሉን ሰላም ለማስፈን ህይወቱን እየሰጠ ከሚገኘው የጸጥታ ሀይል ጎን ተሰልፈን ሰላምን እናሰፍናለን ብለዋል።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በየማህበራችን እቅድ አውጥተን ተወያይተናል ያሉት አመራሮች የሰው ኃይል ስምሪት እያደረጉ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

የእርስ በእርስ መገዳደሉ ሰልችቶናል ያሉት ወጣቶች የከተማችንን ሰላም በማስፈን ለልማት እና እድገት መዘጋጀት አለብን ብለዋል።

ልዩ ተልዕኮ ይዘው በዓሉን ለማወክ የሚመጡ አካላትን በመለየት ለጸጥታ ሀይሉ ፈጣን መረጃ በመስጠት ከተማችንን እንጠብቃለን ሲሉም አክለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top