በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተከበረው የገና በዓል በሠላም መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
በ2018 ዓ.ም የተከበረው የገና በዓል በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ እንደገለጹት የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከጸጥታና የደኅንነት ግብረ-ኃይል ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጎ በመስራቱ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁንገልጸዋል፡፡
የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የክልሉ የፀጥታ ኃይል እና የፀጥታ ግብረ-ኃይሉ ከፍተኛ የሰው ኃይል ስምሪት በማድረግና የበዓሉ አከባባር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሰራቱ በሰላም ማክበር እንደተቻለም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የኃይማኖት አባቶች ፣ለወጣቶች እና ለመላው የክልሉ ህዝብ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ላደረገው ቀና ትብብር እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የክልሉ የፀጥታ ኃይል እና ለደህንነት ግብረ -ኃይል አባላት እና አመራሮች በክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብ በተለይም ወጣቱ የራሱን ሰላም ለመጠበቅ እና ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር እያደረገ ያለው መልካም ተግባር ከፍተኛ በመሆኑ ቀጣይ ለሚከበሩ በዓላትም ትብብሩን እና አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትም ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ አሳስበዋል።

