“የተቀናጀ ስራችሁ ለሀገራችን ተስፋ፣ ለሕዝባችን ደግሞ ጋሻ ሆኗል።” ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

“የተቀናጀ ስራችሁ ለሀገራችን ተስፋ፣ ለሕዝባችን ደግሞ ጋሻ ሆኗል።” ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

በመጀመሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።

ይህንን በዓል ስናከብር፣ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍንና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የጸጥታ ግብረ-ኃይሉ እያከናወነ ያለው ተግባር የታሪክ ማህደር የሚዘክረው ነው።

በተለይም ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን፣ የፌደራል የጸጥታና የደኅንነት አካላት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልላችን ፖሊስ እና የሚሊሻ የሰላም አስከባሪ አባላት እንዲሁም በየደረጃዉ የሚገኙ የክልሉ አመራሮች በአንድ ዓላማና በጋራ ቅንጅት የጠላትን ሴራ በማክሸፍና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ ያለው ፅናት የሚደነቅ ነው።

የጸጥታና ደህንነት ግብረ-ኃይል ቅንጅት፣ የሕዝባችንን የደህንነት ስጋት በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ይህ የተቀናጀ ተግባርም ለሀገራችን ተስፋ፣ ለሕዝባችን ደግሞ ጋሻ ሆኗል።

በዓሉን ስናከብር፣ እነዚህ የሰላም ዘቦች በብርድና በፀሐይ ሳይበገሩ እያደረጉት ያለውን ተጋድሎ በማሰብና ለጸጥታ አካላቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር በማድረግ ሊሆን ይገባል።

ይህ በዓል ለመላዉ ሰራዊታችን እና ለቤተሰቦቻችሁ የደስታ እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ፣ በቀጣይም የጀመርነውን የሰላም ጉዞ ይበልጥ በማጠናከር የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት እንደምናረጋግጥ ጽኑ እምነቴ ነው።

በድጋሚ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።

በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top