በጃቢ ጠህናን ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።
በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ገብተዋል።
ህገ-ወጥ ታጣቂዎቹ የአማራን ሕዝብ ነጻ እናወጣለን በሚል ወደ ጫካ ገብተን በሕዝባችን ላይ የሰላም እጦት እንዲከሰት ምክንያት ኾነናል ብለዋል። የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ እና ለማገልገል መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ መቀበላቸውንም ገልጸዋል።
ሌሎች ህገ-ወጥ ታጣቂዎችም የቀረበውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።




