ፖሊስነት በእውነት የታነፀ ለቆመለት አላማ የፀና የህዝብን እና የሀገርን ንብረት የሚጠብቅ የህዝብ አለኝታ ነው።
ፓሊስ እጁ ንፁህ፣ለተቸገሩት ፈጥኖ ደራሽ ለቆመለት አላማ እና ለገባው የሙያ ቃልኪዳን እራሱን አሳልፎ የሚሰጥ የሀገር ኩራት ነው።
የአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም ዘመናዊ ቴክኖሎጅን የተላበሰ ፣ለሙያው ክብር ያለው በታማኝነት ህዝብን የሚያገለግል እንዲሁም ከሙስና እና ከሌሎች ህገ-ወጥ ተግባሮች የፀዳ የፖሊስ ሰራዊት እየገነባ ይገኛል።
ተቋሙ ያስቀመጣቸውን ህግ እና ደንቦች አክብው ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በታማኝነት በመወጣት ለሰራዊቱ ምሳሌ የሚሆኑ አባሎች እየተፈጠሩም ይገኛሉ።
ለዚህ ምሳሌ ደግሞ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባል የፈፀመው የታማኝነትና የሙያ ክብር ተጠቃሽ ነው።
ኮንስታብል ሁሴን ሙስጠፋ ሰይድ ይባላል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በኬሚሴ ከተማ በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ኦፊሰር ነው።
ኮንስታብል ሁሴን ሙስጠፋ በቀን 30/03/2018 ዓ.ም ከአዋሽ ባንክ ኬሚሴ ቅርንጫፍ 4 መቶ ሺህ (400,000) ብር በስህተት ወደ አካውንቱ ይገባል።
በአካውንቱ የገባውን ገንዘብ የተመለከተው ኮንስታብል ሁሴን ለፖሊስ ሙያ የገባውን የእምነት ቃል እና የሙያ ክብር በማስታወስ ወደ ባንኩ በመሔድ በስህተት የገባውን 4 መቶ ሽህ ብር መመለስ ችሏል።
የአዋሽ ባንክ ኬሚሴ ቅርንጫፍም ፖሊስ ከግል ጥቅሙ ይልቅ የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም የሚያስቀድም በታማኝነት እና በኃላፊነት የሚያገለግል መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።
በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ኡመር መሐመድ ኮንስታብል ሁሴን የፈፀመው የታማኝነት ተግባር የተቋሙን ስምና ክብር ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ሌሎችም ይህንን መልካም እሴት እንደ ተሞክሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል ።
ኮንስታብል ሁሴን ሙስጦፋ ለፈፀመው መልካም ተግባር እና ተቋሙ በሀቀኝነት ህዝብን የሚያገለግል መሆኑን በማሳየቱ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ስም ምስጋና ችረዋል።


