ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ የቀበረው የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አላላ ቀበሌ ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ከአርሶ አደር ማሳ ውስጥ ታጣቂ ቡድኑ ቀብሮት የነበረው የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ጥምር ጦሩ በቁጥጥር ስር አውሎታል።
በዚህም 1155 የዲሽቃ ጥይት 01 የብሬን አፈሙዝ 13 የቃታ መሳሪያዎች መያዙን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።




