የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ልዑካን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ልዑካን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተመድ ተወካዮች ልዑካን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።

የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያው የማኔጅመንት አባላት ለቡድኑ ማብሪሪያ ሰጥተዋል።

ጉብኝቱ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች እና የፎረንሲክ ምርመራ ሂደቶችን ለመመልከት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የወንጀል ምርመራን በሳይንሳዊ መንገድ ለማከናወን የተጀመሩ የፎረንሲክ ላቦራቶሪ ስራዎች እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንም ጎብኝተዋል።

የፖሊስ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ ለመያዝ፣ የወንጀል መዝገቦችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማደራጀት እና አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የተደረጉ ጥረቶችንም ተመልክተዋል።

በተጠርጣሪዎች አያያዝ፣ በምርመራ ወቅት የሚከናወኑ ጥንቃቄዎች እና ሰብዓዊ መብትን መሰረት ያደረጉ የፖሊስ አገልግሎቶችም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር ዳር ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን የምልከታቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑካን አባላት በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባዩት ለውጥ መደነቃቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራን ለማዘመን እና የወንጀል ፍትህ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የልዑኩ አመራሮች በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል።

በተለይም የሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የዲጂታል አሰራርን መዘርጋቱ ለፍትህ ስርዓቱ መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ አብራርተዋል።

የልዑኩ አመራሮች አክለውም ድርጅቱ ለነዚህ የሪፎርም ስራዎች አስፈላጊውን የቴክኒክ እና የሙያ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በጉብኝታቸው መጨረሻ ከክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ጋር በመገናኝት በቀጣይ በትብብር እና አጋርነትን በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የልዑኩ አመራሮች ለሰጡት እውቅናም ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር ) ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top