ታጣቂ ቡድኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ተተኳሾች እና ሎጅስቲኮች መያዛቸው ተገለጸ
በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ በተሬ ቀጠና የተሰማራው ጥምር ጦር ለ3 አመት ዋና ማዕከል በማድረግ ቀጠናውን ለእኩይ አላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች፣ የጦር መሳሪያዎች እና ሎጅስትኮች በቁጥጥር ስር ማድረግ መቻሉን ጥምር ጥሩ አስታውቋል።
በዚህም 3 ሲኖ ትራክ ፣ 2 ፒካፕ፣ 1 ሀርድ ቶፕ፣ 1 ሀይሩፍ አምቡላንስ፣ 01 መትረየስ፣ 2 ጥቁር ክላሽ፣ 7 ክላሽ፣ 8 የቃታ መሳሪያ፣ 360 የክላሽ ጥይት፣ 360 የመትረየስ ጥይት፣ 65 ዲሽቃ ጥይት፣ 9 መገናኛ ሬዲዬ፣ 9 የመገናኛ ቻርጀር፣ 9 F1 ቦምብ፣ 11 የሞርተር ቁቡላ፣ 1 ግሪደር እና 2 ሎደር እንዲሁም 12 ባጃጅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
በተጨማሪም የመኪና መለዋወጫ እና ሌሎች ቡድኑን ሊጠቀምባቸው የነበሩ ሬሽኖች በጥምር ጦሩ ገቢ መሆናቸውን ነው የቀወት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያስታወቀው።








