የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የዲጅታላይዜሽን ጉዞ በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የዲጅታላይዜሽን ጉዞ በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ

የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እንድሪስ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ እና የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ድኤታ ኸይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተከናወኑ የዲጅታላይዜሽን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተመልክተዋል።

ጉብኝቱ የፖሊስ አገልግሎትን ለማዘመን እና የወንጀል መከላከል ስራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

የክትትል ካሜራዎችን እና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የክልሉን ሰላም የማስከበር ስራን፣ በከተሞች እና ቁልፍ ቦታዎች ላይ የሚደረጉ የጸጥታ ክትትል ስራዎች በቴክኖሎጂ የታገዙ ስለመሆናቸው የስራ ኃላፊዎች ተመልክተዋል።

በተጨማሪም ዲጂታል መረጃ አያያዝን፣ የወንጀል መዝገቦችንና የተጠርጣሪዎችን መረጃ በዘመናዊ ዳታቤዝ የማደራጀት ስራን እንዲሁም ፈጣን አገልግሎት በመስጠት የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለጥሪዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የተዘረጉ መሰረተ-ልማቶችን እና ቁልፍ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ነው በጉብኝቱ ወቅት የስራ ኃላፊዎቹ የተመለከቷቸው።

የስራ ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ የፖሊስ ተቋም ራሱን በቴክኖሎጂ ማዘመኑ ወንጀልን በሳይንሳዊ መንገድ ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል።

በክልሉ ፖሊስ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች አበረታች መሆናቸውንም የጉብኝቱ ተካፋዮች አክለው ገልጸዋል።

የፖሊስ ተቋም ራሱን በቴክኖሎጂ ማዘመኑ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ በጉብኝቱ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በበኩላቸው የተጀመሩ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች የሰው ኃይልን በብቃት ለመምራት እና የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽነት፣ ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማከናወን የሚያስችሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል እና ምርመራ ስራውን በዲጂታል በማዘመን ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር ግንኙነቱን አጠናከሮ ስራዎችን በመስራት በዘመናዊ ዲጂታል ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top