ዘላቂ ሰላም እና ደኅንነት የሚረጋገጠው ማኅበረሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅቶ ሲሰራ እንደሆነ ተገለጸ።

ዘላቂ ሰላም እና ደኅንነት የሚረጋገጠው ማኅበረሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅቶ ሲሰራ እንደሆነ ተገለጸ።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በህግ ማስከበር ስራዎች እና በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አብዱ ሁሴንን ጨምሮ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ውይይቶችን አካሂደዋል።

በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እና የማህበረሰቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ የጸጥታ ኃይሉ መስዋትነት እየከፈለ እንደሚገኝ በውይይቱ ተጠቅሷል።

የክልሉ የጸጥታ ኃይል የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ተጠናክሮ እየሰራ ቢሆንም ሁሉም የድርሻውን ካልተዋጣ የጸጥታ ኃይሉ ብቻ ሰላም ማምጣት እንደማይቻልም ተጠቁሟል።

ባለፉት ዓመታት የነበረው የሰላም መደፍረስ የብዙዎችን ህይወት ያሳጣ፣ ኢኮኖሚ እና ልማትን ያወደመ እንደነበርም ተጠቅሷል።

ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ማኅበረሰቡ ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጎን እየቆመ ማገዝ፣ በውስጡ ተሰግስገው ለስቃይ የሚዳርጉትን መክሮ እንዲመለሱ ማስቻል እንዲሁም አሻፈረኝ የሚሉትን ደግሞ ለራሱ ደኅንነት ሲል ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ በተካሄዱ የውይይት መድረኮች ተጠይቋል።

አርሶ አደሮች በሰላም እያረሱ አይደለም፣ ነጋዴዎችም እንደልብ አይተዘዋወሩ እየነገዱ እንዳልሆነ የተናገሩት የውይይት ተሳታፊዎች እናቶች እና ሕጻናትም ነገ ምን ይገጥመን ይሆን እያሉ የዘወትር ጭንቀት ላይ መሆናቸውንም አክለዋል።

ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ማኅበረሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ አካባቢውን በንቃት ሲጠብቅ እንደሆነም ተገልጿል።

የተረጋገጠ ሰላም ለመገንባት የጸጥታ ችግሮችን በሰከነ ውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እና በሙሉ አቅም ወደ ልማት ለመግባት ተቀራርቦ መነጋገር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ግጭት የወለደው የኑሮ ውድነት ሕዝቡን ፈትኖታል፤ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ሰርቶ የዕለት ጉርስ ማግኘትም ሆነ ልጅ ማሳደግ ከባድ እንዲሆን ያደረገውን የሰላም መደፍረስ በሰከነ ሁኔታ መፈታት አለበት ተብሏል።

የመንግስት አቋም ሀገራዊ አንድነት ተጠብቆ እና ሰላም አስፍኖ ሀገራችን እንድትለማ ውስጣዊ ልዩነቶቻችንን በውይይት መፍታት ያስፈልገናል ሲሉ ተናግረዋል።

የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችም ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ሲሉ በሀቅ ላይ የተመሰረተ ንግግር ማድረግ እና ለእርቀ ሰላም መሸምገል አለባቸው ተብሏል።

የሁሉም ሀይማኖት አባቶች ስለ ሰላም ማስተር፣ ስለ አንድነት መስበክ እና ለሀገር ሰላም ሲሉ ግፍን ተጸይፈው ‘ህዝቤን አደራ’ ብለው ያለፉትን አቡነ ጼጥሮስን አርዓያ በማድረግ እስከ መስዋዕትነት የሚዘልቅ ተግባርን መወጣት ይገባል ተብሏል።

ከሀገር ወግ እና ባህል ወጥተው የሀገር ሽማግሌዎችን የእርቅ ልመና የሚገፉ ሲገኙ ደግሞ ህዝብ ሰላም ውሎ ያድር ዘንድ መንግስት ህግ እንዲያስከብር በማለት ተወያዮቹ ጠይቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top