ለታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ህገ-ወጥ መሳሪያ እና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ለታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ህገ-ወጥ መሳሪያ እና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ አዲስ ቅኝ ቀበሌ ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ በወረዳው ጥምር ጦር ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን በዞኑ የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጸሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር አድማሱ ገላዬ ተናግረዋል።

የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አማ -35960 በሆነ ተሽከርካሪ የክላሽ መሳሪያ ከ9 ሺህ በላይ የብሬ እና የክላሽ ጥይቶችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ መያዙን ነው ኢንስፔክተር አድማሱ አክለው የገለጹት።

ህገ-ወጥ መሳሪያውን እና ተተኳሹን ሲያጓጉዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም አዛዡ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ታጣቂ ቡድኑ ሲገለገልባቸው የነበሩ ሁለት ሞተር ሳይክል እና ስድስት ባጃጆችንም በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም ኢንስፔክተር አድማሱ ገላዬ የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጸሕፈት ቤት አዛዥ አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top