‘የምርጫ ደኅንነት እና የጸጥታ ተቋማት ሚና’ መፅሐፍ ሽያጭ ለጀግኖች ማዕከል ግንባታ እንዲውል ተበርክቷል።

‘የምርጫ ደኅንነት እና የጸጥታ ተቋማት ሚና’ መፅሐፍ ሽያጭ ለጀግኖች ማዕከል ግንባታ እንዲውል ተበርክቷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ‘የምርጫ ደኅንነት እና የጸጥታ ተቋማት ሚና’ በሚል ርዕስ የጻፉት መፅሐፍ ተመርቋል።

መጽሐፉ ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ ተዘጋጅቷል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ‘የምርጫ ደኅንነት እና የጸጥታ ተቋማት ሚና’ መፅሐፍ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ጀግኖች ማዕከል ማገገሚያ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ለአማራ ክልል ጀግኖች ማዕከል ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top