“ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተሻግራ ጸንታ እንድትቆም የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት መስዋዕትነት ከፍለዋል!” ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ ሚካኤል

“ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተሻግራ ጸንታ እንድትቆም የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት መስዋዕትነት ከፍለዋል!” ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ ሚካኤል

የጸጥታ እና ደኅነንት ተቋማት የምስጋ እና የእውቅና ፕሮግራም ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ ሚካኤል የምስጋና መርሃግብሩ ላይ እንደገለጹት “ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተሻግራ ጸንታ እንድትቆም የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት መስዋዕትነት ከፍለዋል!” ብለዋል።

ኮሚሽነር ጀኔራል ባለፉት ጊዜያት በሀገራችን የተካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ በዓላት እና ኮንፈረንሶች በስኬት እንዲጠናቀቁ የጸጥታ እና ደኅንነት አካላት በቅንጅት ላከናወኗቸው ተግባራት በራሳቸውና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የውጭ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ በርካታ ጋዜጠኞች እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች የተሳተፉባቸው ትላልቅ ጉባኤዎች እና ኮንፈረንሶች ያለ አንዳች እንከን በስኬት መጠናቀቃቸው ሀገራችን በዲኘሎማሲው መስክ ከፍተኛ ድል እንድትጎናጸፍ ከማስቻሉም በላይ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተሰሚነት እና ክብር እንድታገኝ አስችሏታል ነው ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራሉ።

ለዚህ ስኬት የበቃነው በሀገራችን የተካሄዱ የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት ሪፎርም ስኬታማ ሆኖ ተቋማቱ ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣታቸው መሆኑንም ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ ሚካኤል አስታውቀዋል።

አሮጌ እና ኋላቀር አስተሳሰቦች ተወግደው እንደሀገር ውስጣዊ አንድነታችን እና ጽናታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የትኛውም ዓይነት ችግርና ፈተና ሳይበግረን የሀገራችን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል የሕዝባችን አለኝታ ሆነን ተልዕኳችንን በአስተማማኝ ሁኔታ በመወጣታችን ነው ሲሉም ኮሚሽነር ጀኔራሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

የውስጥ ባንዳዎች እና የውጪ ባዳዎች ሀገራችንን ችግር ውስጥ ለማስገባት በተለያዩ ጊዜ የሚያደርጉትን ሙከራ በማክሸፍ የሀገራችን ሰላም በማረጋገጥ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት የሰሯቸው ብዙ ገድሎች መኖራቸውንም አንስተዋል።

በቀጣይ የፀረ ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ በማክሸፍ እና በየቦታው የተበታተኑትን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት የሀገራችን የውስጥ ሰላም ከመቸውም ጊዜ በላይ ማረጋገጥ የምንችልበት ምዕራፍ ላይ ስለደረስን ሁላችንም ከዚህ በፊት ከሰራነው በበለጠ ደረጃ ተቀናጅተን መስራት ይኖርብናል በማለት ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ ሚካኤል የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የምስጋና መርሃግብሩ ‘ጠንካራ የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ’ በሚል መሪ ቃል መካሄዱን ነው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያስታወቀው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top