ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጅ ተጠቅሞ ለሚከሰቱ ውስብስብ እና ረቂቅ ወንጀሎች ምላሽ የሚሰጥ የፖሊስ ሰራዊት እየተገነባ ነው!

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጅ ተጠቅሞ ለሚከሰቱ ውስብስብ እና ረቂቅ ወንጀሎች ምላሽ የሚሰጥ የፖሊስ ሰራዊት እየተገነባ ነው!

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ5 ቀጠናዋች ሲሰጥ የቆየውን የጂኦ ስትራቴጅካዊ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና መጠናቀቅን አስመልክቶ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚችል በፖሊሳዊ ስነ-ምግባሩ የተመሠከረለት እና አድሎአዊ አሰራርን የተጸየፈ የፖሊስ አመራር እና አባላት ለመገንባት የተሰጠው ስልጠና ውጤት የታየበት መሆኑን አስታውቀዋል።

በአምስቱም ቀጠናዎች የተደረገው የስልጠና ሰነድ ክፍት በመሆኑ ሁሉም አባል ለተቋሙ ያለውን ሀሳብ በነጻነት የገለጸበት፣ በአመራሩና በአባላቱ መካከል የነበሩ የረጅም ጊዜ የሻከሩ የግንኙነት ሰንሰለቶች የተሰበሩበት እና ግርታ የሚፈጥሩ ጉዳዮችን በጋራ የፈታንበት ሆኗል ብለዋል።

ተቋማዊ የለውጥ ስራዎች ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆኑ የጋራ አስተሳሰብ እና የጋራ አቋም እንዲኖር ያደረገ እንደሆነም አክለዋል።

ስልጠናው እውቀትን የተቀያየርንበት እና የኢንዶክትሬሽን ስራዎችን ያጎለበትንበት በመሆኑ የተፈለገውን ግብ ያሳካ እና ለፖሊስ ሰራዊቱ ትልቅ አቅም የፈጠረ ከፍተኛ ቁጭት እና መነሳሳትም የታየበት እንደሆነ አመላክተዋል።

በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች ጠቃሚ እና ለጀመርነው ተቋማዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ለሚከሰቱ ውስብስብ እና ረቂቅ ወንጀሎች ምላሽ የሚሰጥ የህብረተሰቡን ጥያቄ ተረድቶ ተገቢውን አግልጋሎት የሚሰጥ የፖሊስ ሰራዊት እየተገነባ እንደሚገኝም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

እንደ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለጻ የፖሊስ ሙያን ልትወደው እና በውስጥህ ሰርጾ ሊገባ እንዲሁም ሁሌም እራሱ መስዋትነትን እየከፈለ የህዝብን ሰላም የሚያረጋግጥ የሰላም ዘብ ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ሰራዊት የሀገርን እና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ህዝብን በታማኝነት ማገልገል እና ለቆመለት ዓላማ ኃላፊነትን መወጣት የሚችል እንደሆነም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊነት ስሜትን እና የህዝብ ፍቅርን ተላብሶ ሙያዊ ግዴታውን የሚወጣ ፖሊስ እየተገነባ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

አሁን ያለው የአማራ ክልል ፖሊስ ተቋማዊ አደረጃጀት ከማንኛውም ጣልቃ ገብነት የጸዳ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኝ የፖሊስ ሰራዊት የተቀበለውን ሙያዊ ኃላፊነት በታማኝነት እና በቅንነት በመወጣት ተቋሙን የማሳደግና የህብረተሰቡን ሰላም የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎበታል ሲሉም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን የሚወጣና ውሳኔ ሰጪ የህግ የበላይነትን አስከባሪ ፖሊስ ለመገንባት ስልጠናው ትልቅ አቅም ፈጥሯልም ብለዋል።

በጂኦ ስትራቴጅካዊ ቁመናችን ላይ የተነሱት ጉዳዮች የቅርብ ስጋቶቻችንን እና የሩቅ ጠላቶቻችንን የለየንበት ባዳዎች እና ባንዳዎች ተቀናጅተው ሀገራችን ለማተራመስ እያደረጉት ያለውን ሴራ ያወቅንበት የስልጠና መድረክ ነው ሲሉም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሰራዊታችን ለምን መስዋዕትነትን እንደሚከፍል በግልጽ የተረዳበት እና ሰላምን ለማስከበር እየታገለ እንደሚገኝ ግልጸኝነትን ፈጥሯል ብለዋል።

ለሰበዓዊ ፍጡር ከለላ የሚሆን፣ ከአድሎአዊ አሰራር የጸዳ፣ ሀገራዊ ስሜት በውስጡ የገዘፈ እና በአስተሳሰቡ የላቀ የፖሊስ ሰራዊት እየተገነባ እንደሚገኝም ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

የክልሉን ብሎም የሀገሩን ደህንነት ለማስከበር ህይወቱን እየሰጠ ለሚገኘው ሰራዊት ሊርበው እና የሚለብሰው ማጣት የለበትም ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ እና የተሟላ ሬሽን ለማቅረብ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ሚዲያ ፖሊስ እና ህብረተሰቡ ተቀራርቦ እንዲሰራ፣ የተሳለጠ የወንጀል መከላከል ስራ እንዲኖር እና ተቋሙ የጀመራቸውን የለውጥ ስራዎች ተከታትሎ ለህዝብ በማድረስ እያደረገ ያለው ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሁሌም የፖሊስ ስራዎች ለህዝብ እንዲደርሱ ከጎናችን የማይለየው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዲሁም የክልል አመራሮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች እና የፖሊስ አመራሮች በአምስቱም ቀጠና የተካሄደው ስልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ትብብር እና ለሰጡን ክብር እንዲሁም ሁሌም ሰላም እንዲመጣ ከፖሊስ ጎን ሆኖ አጋርነቱን በተግባር እያሳየን ላለው የአማራ ህዝብ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በሰጡት መግለጫ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top