የጅኦ-ስትራቴጂካዊ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚወስዱ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት የልማት ስራዎችን ጎበኙ

የጅኦ-ስትራቴጂካዊ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚወስዱ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት የልማት ስራዎችን ጎበኙ

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጎጃም ቀጣና ፖሊስ አመራሮች እና አባላት የጂኦስትራቴጂክ እና የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠናን በአማራ ክልል ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ስልጠናውን መከታተሉ የቆዩ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነቡ እና በግንባታ ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል።

የማዕድ ምግብ ኮምፕሌክስ አክሴዮን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አለምሸት ቢያዝን የፖሊስ ሰራዊቱ በሚከፍልው መስዋትነት በከተማዋ በርካታ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን የገለጹት በጉብኝቱ የተሳተፉ ሰልጣኝ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ ሰላምን በማረጋገጥ እና ህግ በማስከበር የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top