በምዕራብ በለሳ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገቡ!

በምዕራብ በለሳ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገቡ!

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት(አፋሕድ) መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ በለሳ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 65 የታጠቁ ቡድኖች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ሙሉ ትጥቃቸውን ለመንግስት በማስረከብ በሰላም ገብተዋል።

የሰላም አማራጭን በመቀበል ለገቡ የታጣቂ ቡድኑ አባላት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አመራር አቶ ጀንበሩ ሞላ፣ የምዕራብ በለሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ አዛናው እና የ57ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ ከፍያለው አያናው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሰላም ስመምምነቱን ተከትሎ በሰላም የገቡ ታጣቂዎች የተፈረመው የሰላም ስምምነት የክልሉን ህዝብ ዘላቂ ሰላም እና ልማት በማረጋገጥ ጥያቄዎችን የሚመልስ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሌሎች በጫካ ያሉ ወገኖችም የእነሱን ፈለግ በመከተል እና መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል እንዲሁም ለህዝብ ሰላም እና ደኅንነት መረጋገጥ የስምምነቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top