“ለህግ የበላይነት መከበር እና ለህዝብ ሰላም መረጋገጥ የመረረ ትግልና የሰከነ የአስተዳደር ጥበብን መላበስ ለነገ የማይተው ጉዳይ ነው!” ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ

“ለህግ የበላይነት መከበር እና ለህዝብ ሰላም መረጋገጥ የመረረ ትግልና የሰከነ የአስተዳደር ጥበብን መላበስ ለነገ የማይተው ጉዳይ ነው!” ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ

የአማራ ክልል የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የክልሉን አሁናዊ የጸጥታ ሁኔታ ገምግሟል።

በአማራ ክልል እየተስተዋሉ ያሉ የህግ አለመከበር እና የሰላም አለመረጋገጥ ችግሮችን በማስተካከል “ለህግ የበላይነት መከበር እና ለህዝብ ሰላም መረጋገጥ የመረረ ትግልና የሰከነ የአስተዳደር ጥበብን መላበስ ለነገ የማይተው ጉዳይ ነው!” ሲሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ ተናግረዋል።

ክልሉን አውዳሚ ግጭት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን አሁን ያለበት ቁመና ከመዋጋት ይልቅ ዘረፋና የውሸት ፕሮፓጋንዳ ላይ ያተኮረ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችን ነጻ በማውጣት እና የህዝብ አገልግሎት እንዲቀጥል ለማድረግ በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ኮሎኔል ተሾመ አስማማው በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ ኃላፊ በበኩላቸው የክልሉ የጸጥታ ኃይልና መከላከል ሰራዊት በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ አንጻራዊ ሰላም መመዝገቡን ጠቅሰው በበርካታ አካባቢዎች ውስጥ አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥና ከስጋት ነጻ የሆነ ክልልን ለመፍጠር በህግ ማስከበር ተግባር ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የተጀመረውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጡ ነው ያሉት ኮሌኔል ተሾመ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተገቢው የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራት ይኖርበታል ሲሉም አክለዋል።

ባህርዳር ከተማ ውስጥ ይስተዋሉ የነበሩ የወንጀል ድርጊቶችን መቀነስ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም የአማራ ክልል የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ በገመገመበት ወቅት አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top