ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገለጸ።

ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገለጸ።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ በርካታ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል እና ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዝ መቻሉን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የአቢሻገር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር ሁሴን መብራቱ ገልጸዋል።

ከኮንትባንድ ዕቃዎች በተጨማሪ የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ ልዩ ልዩ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከአጋር የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገ የኬላ ፍተሻ መያዛቸውን ኢንስፔክተር ሁሴን መብራቱ አስታውቀዋል።

ፖሊስ የህብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ በሚያደርገው የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ተግባር ከ350 በላይ የሚሆኑ ህገ-ወጥ ስደተኞች እንደተያዙም አዛዡ ጠቁመዋል።

እንደ ፖሊስ አዛዡ ገለጻ ህገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ እና በህዝብ ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

ከህገ-ወጥ ድርጊቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በተያዙ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

የከተማውን ሰላም ለመጠበቅ ቀን እና ሌት ከፖሊስ ጋር ተቀናጅቶ የወንጀል መከላከል ስራ እየሰራ ለሚገኘው ማህበረሰብ ምስጋና ያቀረቡት የፖሊስ አዛዡ ቀጣይ የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረጉ የወንጀል መከላከል ተግባራት አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top