የዞኑ የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት እያደረገ ባለው ህግ ማስከበር አንፃራዊ ሰላም ማምጣት መቻሉን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት እያደረገ ባለው ህግ ማስከበር አንፃራዊ ሰላም ማምጣት መቻሉን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በእርስ በርስ ግጭቱ የተነሳ በህገ- ወጥ ታጣቂዎች ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎችን ለመከላከልና ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ የዞኑ የፀጥታ ሀይል ከፌደራል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት ባደረገው ትግል አንፃራዊ ሰላም ማምጣት መቻሉን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ፋንታ ተጋፋው ገልፀዋል።

የዞኑ ፖሊስ ሰራዊት ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በሚያደርጋቸው የህግ ማስከበር ስራዎች መስዕዋትነት እየከፈለ የህዝቡን ሰላም ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራሩን በማጠናከር ውጤታማ ተግባር እየከወነ መኾኑን የገለጹት አዛዧ በሰላም ማስጠበቅና ህግ ማስከበር ተግባር ተዋጊም ሰላም አስከባሪም የሆነ የፖሊስ ሀይል ተፈጥሯል ብለዋል።

ቀደም ሲል በዞኑ የሚገኙ የተወሰኑ አካባቢዎች በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ነበሩ ያሉት ኮማንደር ፋንታ አሁን ላይ እየተደረጉ በሚገኙ የህግ ማስከበርና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ቀጠናዎችን ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ትኩረት ሰተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ለመከላከልና ህብረተሰቡን ከገጠመው የፀጥታ ችግርና የመልካም አስተዳደር እጦት ለማላቀቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ እንደሚገኙም ኮማንደር ፋንቱ ጠቁመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top