የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ያሰለጠናቸውን ምልስ የፖሊስ አመራሮችንና አባላትን አስመረቀ።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የስነ-ምግባር ችግር ሳይኖርባቸው በልዩ ልዩ ምክንያቶች የፖሊስ ተቋምን ለቀው የነበሩ የፖሊስ አመራሮችና አባላትን ነው ያስመረቀው።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሰቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ እና የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም መምህራንና አሰልጠኞች በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የአካዳሚክስ ጉዳዩች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሸነር ግዛቸው ከበደ ባቀረቡት የስልጠና ሪፖርት እንደተመላከተው ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ እና ወቅታዊ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ ያገናዘበ የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ የክልላችን ፖሊሰ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አደረጃጀት ሰርቶ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በመዘርጋት እየተተገበረ የሚገኝ በመሆኑ ለውጡን በማቀጣጠልና የተጀመሩ ስራዎችን በቁርጠኝነት በመፈጸም ተቋማችሁን የምትክሱበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የፖሊስ ሰራዊቱን የመፈጸም አቅም በማሳደግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ሲሉ ነው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ያብራሩት።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ኃይል ልማት አስተዳደር ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ዳግም የሰጣችሁን እድል ተጠቅማችሁ ህዝብን በታማኝነት እና በቅንነት ማገልግል ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወደ ተቋሙ እንዲመለሱ ድጋሜ እድሉን በማግኘታቸው ምስጋና ያቀረቡት የዕለቱ ተመራቂዎች ካለፈው ስህተት ተምረን ህዝባችን ለማገልግል እና ለመካስ ዝግጁ ነን ሲሉ አክለዋል።
በመጨረሻም በቀጣይ ለሚሰጣችዉ ማንኛውም ተልዕኮ እና ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን ነው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ያስታወቁት።









