የኤች.አይ.ቪ ኤዲስ የፖሊስ ሰራዊት የጤና ችግር እንዳይሆን ቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።

የኤች.አይ.ቪ ኤዲስ የፖሊስ ሰራዊት የጤና ችግር እንዳይሆን ቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።

የአለም የኤዲስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ37ኛ ጊዜ መከበርን ምክንያት በማድረግ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የተገኙ ሲሆን የፖሊስ ሰራዊቱ ዘርፈ ብዙ ተልዕኮ ያሉት በመሆኑ ጤናማ ሰራዊት መፍጠር ቀዳሚው ተግባር በመሆኑ ኤች.አይ.ቪ ኤዲስ በሽታ ላይ ያተኮረ ግንዛቤን በማሳደግ የበሽታውን ስርጭት መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

የፖሊስ ተቋም ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ በመሆኑ ከወንጀል መከላከሉ ጎን ለጎን የማህበረሰቡንና የራሱን ግንዛቤ በማሳደግ የኤች.አይ.ቪ ኤዲስ ስርጭትን መከላከል እንደሚገባም ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

ኤች.አይ.ቪ ኤዲስ የፖሊስ ሰራዊቱ የጤና ችግር እንዳይሆን የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባሮች እያከናወን እንገኛለን ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ በቀጣይም ከሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ጋር ተቀናጅተን በመስራት በሰራዊታችን ላይ እየታየ ያለውን መዘናጋት ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኤች አይ ቪ ኤዲስ ሜኒስትሪሚንግ ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ደስታ መራዊ በበኩላቸው አሁን ላይ በኤች.አይ.ቪ ኤዲስ እየታየ ያለው መዘናጋት የብዙ ሰዎችን ህይወት እያሳጣን በመሆኑ የትኛውም የማህበረሰብ ክፍል ትኩረት ሰጥቶ እራሱንና ሌሎችን ከበሽታው መጠበቅ ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በ2030 ኤች.አይ.ቪ ኤዲስ የማህበረሰብ የጤና ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ማድረስ የሚል እቅድ እንደተያዘ የገለፁት አቶ ደስታ መራዊ እቅዱን ለማሳከካትም ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ውይይትና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የፖሊስ ሰራዊቱ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ የሰላም ዘብ በመሆኑ ለኤች.አይ.ቪ ኤዲስ ተጋላጭ እንዳይሆን በየደረጃው የሚገኝ አመራር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም አቶ ደስታ ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኩ ግልፅነትን በሚጠይቁ ጉደዮች ዙሪያ ከተወያዮች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አስፈላጊው መልስና ማብራሪያ ከመድረክ መሪዎቹ ተሰጥቶባቸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top