በርካታ የህገ ወጥ ቡድኑ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው እጅ ሰጡ።
በምዕረብ ጎንደር ዞን ለአመታት ህብረተሰቡን በመዝረፍ፣ በመግደል እና በማፈናቀል እኩይ ተግባር ውስጥ ተሰማርተው የቆዩ 14 የህገ ወጥ ታጣቂው አባላት የቡድኑን የጥፋት ሴራ በመቃወም ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር እጅ ሰጥተዋል።
በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ብርጋዲዬር ጄኔራል ቾምቤ ወርቁ ህገ ወጦቹ የሠላም ጥሪ ተቀብላችሁ ለሠላም ቅድሚያ በመስጠት ለሠራዊታችን እጅ መስጠታችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል።
ከሠላም አማራጭ ውጭ የጥፋት ተልዕኮ በሚፈፅሙት ላይ እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ብርጋዲዬር ጄኔራል ቾምቤ ወርቁ ተናግረዋል።
እጅ የሰጡ የህገ ወጥ ቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያየት መጀመሪያ የገባነው በጥፋት ቡድኑ የተሳሳተ የውሸት ፕሮፖጋንዳ በመታለል ነው አሁን ግን የቡድኑን ሴራ ከተረዳን በኋላ ጥለን ለመውጣት ተገደናል ብለዋል።
እጅ የሠጡ ህገ ወጥ አባላት በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ወደ ሠላም እንዲመጡና እጅ እንዲሠጡ ጠይቀዋል።





