ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑን ለማስታጠቅ መነሻው ባህር ዳር ከተማ መዳረሻውን ደግሞ ደሴ ከተማ ለማድረግ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አማ 31439 የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አይ ሱ ዙ መኪና 1 ድሽቃ መሳሪያ ከቻንሲው ጋር በማሰር ጭኖ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከነ ግብረ አበሮቹ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት በቀጠናው ከሚገኘው የዕዙ መሃንዲስ ክፍል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋል።
ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ እንደ ሎጀስቲክስ ሆነው የሚያገለግሉ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑን ለማስታጠቅ የሚደረገው ሙከራ እንደማይሳካና በቀጣይ የሚደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በቀጠናው የሚገኙ የክፍሉ አመራሮች መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


