ዕዙ የውጭ ጠላቶችን አጀንዳ የሚያመክን ሕገ መንግሥታዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው።

ዕዙ የውጭ ጠላቶችን አጀንዳ የሚያመክን ሕገ መንግሥታዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው።

‎‎በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ሕገ መንግሥታዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ መኾኑን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ አስታውቀዋል።

የዕዙ ዋና አዛዥ ከኮር፣ ከክፍለ ጦር እና ከዕዝ ከፍተኛ መሪዎች ጋር በወቅታዊ የግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ መክረዋል። በምክክሩም የቀጣይ የሕግ ማስከበር አፈፃፀም አቅጣጫም ተሰጥቷል፡፡

ዕዙ በአማራ ክልል ከተሰማራ ጀምሮ የውጭ ጠላቶችን አጀንዳ አስፈፃሚዎችን ሴራ በመረዳት ፍላጎታቸውን የሚያመክን ሕገ መንግሥታዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ዕዙ በተሰማራባቸው የጎጃም ዞኖች ኅብረተሰቡ ዘላቂ ሰላሙን እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የሠራዊቱ መሪዎች ግዳጁ የሚጠይቀውን የመሪነት ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ተብራርቷል፡፡

የታጠቁ ኀይሎች ኅብረተሰቡን በመዝረፍ የአንዳንድ የአካባቢውን የጸጥታ አካላት እና የመንግሥት ሠራተኞች ቤተሰቦችን በማገት፣ በማንገላታት፣ በዛቻ እና ማስፈራሪያ የማይገባ ተግባር መፈጸማቸውንም ዋና አዛዡ ገልጸዋል።

ሕዝቡም ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነም ተመላክቷል።

የተጀመሩ የመሠረተ ልማቶችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማድረግ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እየሰጠም ይገኛል ብለዋል፡፡

ሠራዊቱ እንደተለመደው በኀላፊነት እና ተጠያቂነት ስሜት በቀጣናው የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ለባዕዳን አሳልፎ ለመስጠት ያሰፈሰፈውን የውስጥ ባንዳ በማጽዳትም ሠራዊቱ ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንዳለበት ነው በውይይቱ የተነሳው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top