“በፍትሕ እጦት ለተቸገረው የክልላችን ህዝብ ተግተን በመስራት ስብራቱን መጠገን ይጠበቅብናል።”አቶ ብርሐኑ ጎሽም

“በፍትሕ እጦት ለተቸገረው የክልላችን ህዝብ ተግተን በመስራት ስብራቱን መጠገን ይጠበቅብናል።”አቶ ብርሐኑ ጎሽም

በአማራ ክልል አዲስ ለተመደቡ ከ1መቶ በላይ የአቃቤ ህግ አባላት የስራ መመሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መርሃ-ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም እንደተናገሩት “በፍትህ እጦት እየተቸገረ የሚገኘውን የክልላችን ማህበረሰብ ለመካስና ለመጠገን ተግተን መስራት ይኖርብናል” ብለዋል።

ስልጠናው የፍትህ ተቋሙን ዓላማ፣ የማህበረሰቡን የፍትህ ፍላጎት የተረዳ፣ በስነምግባሩ የታነፀ እና እስከታች ድረስ ወርዶ መስራት የሚችል ባለሙያ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑንም ነው አቶ ብርሃኑ ጎሽም የገለፁት።

በብልሹ አሰራሮች እና ባልተደራጁ የመረጃ አያያዝ ምክንያት የህዝባችን የሚፈልገውን ፍትህ ሳያገኝ ቆይቷል ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለመቅረፍ ከአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጋር በቅርቡ በተፈራረምነው የጋራ ስምምነት ሰነድ መሰረት ከክልሉ ፖሊስ እና ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ፈጣንና ፍትሐዊ የሆነ የፍርድ ውሳኔ በመስጠት ፍትህ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ሲሉም አክለው ተናግረዋል።

ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚቆይም ኀላፊዉ ጠቁመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top