ከፍተኛ አመራሮች በምስራቅ ጎጃም ዞን ህግ በማስከበር ላይ የሚገኙ የጥምር ጦሩ የሰራዊት አባላትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ከፍተኛ አመራሮች በምስራቅ ጎጃም ዞን ህግ በማስከበር ላይ የሚገኙ የጥምር ጦሩ የሰራዊት አባላትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የምስራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች በጎዛመን ወረዳ ጭምት በረሀ ኦፕሬሽን እየሰራ የሚገኝውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአድማ መከላከል ፖሊስ እንዲሁም የሰላም አስከባሪ እና የሚሊሻ አባላትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በስፍራው የተገኙ አመራሮች የወገን ጦርን በማበረታታት የቀጣይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የአድማ መከላከል ፖሊስ ከሀገር መከላክያ ሰራዊት፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጥምር የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ህገ-ወጥ ቡድኑ ላይ እርምጃ በመውሰድ ይጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የ36ኛ ሻለቃ አድማ መከላከል ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር በሪሁን ውዱ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top