ኢትዮጵያ በሞሮኮ ሀገር ማራካሽ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ93ኛው የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው
ኢትዮጵያ በሞሮኮ ሀገር ማራካሽ ከተማ እ.ኤ.አ ከህዳር 24 እስከ 27 ቀን 2025 እየተካሄደ በሚገኘው 93ኛው የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።
በክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራው ልዑካን ቡድን በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ እየተካሄደ ባለው 93ኛው የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጉባኤው ጎን ለጎን ከሞሮኮ ብሔራዊ ደኅንነት ጀነራል ዳይሬክተር አብደላቲፍ ሃሙቺ ጋር ሁለቱ የሕግ አስከባሪ ተቋማት በጋራና በትብብር አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የሁለቱ ሀገራት የሕግ አስከባሪ አካላት የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ዋና ዓላማ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ በስልጠና እና በፀጥታ ማስከበር ዙሪያ አብሮ በትብብር ለመስራት እንደሆነ ታውቋል።








